Episoder

  • ሮማናት – ናሽናል ካፌ . . .

    ሮዝ አገሯ ያለ ካፌ ስትቀጥረኝም ሆነ ቀጥራኝ ስትቆይ ለመጀመሪያ ግዜ ነው ። እንደደረስኩ ወፍራም የማሽን ቡና አዝዤ እሱን እየጠጣሁ ጥበቃዬን ጀመርኩ ። ካፌው ውስጥ ዝንቦች እንዳያስቸግሩ በሚል በየጠረጴዛው የሊም ቅጠል ተነጥፏል ። ውስጥ የሚተራመሰውን ሰው ...

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • Manglende episoder?

    Klik her for at forny feed.

  • የ መ ን ታ ፡ እ ና ት ፡ ፖ ለ ቲ ካ

    [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ]

    ለማበጠር ጀምራው ከነበር ፀጉሯ ውስጥ እጇን ወትፋ "ዋ………ይ"ብላ ጮኸች ። እሪታዋ ርዝመቱ በመሃል ቅላፄዋ እስኪለዋወጥ ነበር ። ጩኸቷን ተከትሎ ቤቱ ውስጥ ፀውታ (*ፀጥታ + ክውታ) ሰፈነ ። የድንገት ጩኸቷ ከሷ በፊት ሲርገበገቡ የነበሩ ሁለት የመንትዬ እንጥሎችን አርግቧል ።

    ሣራ ያለግዜ የመጣችባት ፅጌዋ(*ፔሬዷ) ምቾት ነስታት ድምፅ የሚባል ነገር መስማት አስጠልቷታል። አንዴ አግና በለቀቀችው ጩኸቷ ያሰፈነችውን ፀውታ ቶሎ ለመጠቀም አሰበች ።

    ከጆንያ ላይ ሃባ ክር መዛ ልጆቿ የተጣሉበትን ፊኛ የኮመዲኖው ጠርዝ ላይ ቋጠረችው። ድምር ለቅሷቸው ሲያስጨንቃት ወላ ፊኛውን መደንቆል ዳድቷት ነበር ።… ጧ! አርጋ አፈንድታ - ሠላሟን ያገኘች እንደው - ግን መጮህን መረጠች ።

    ፊኛው ላይ እንደማይደርሱ ያወቁት አልቃሻ ልጆቿ በድንገቴ ቃጠሎ ጩኸቷ ተደናግጠው ለአፍታም ቢሆን እንደማደብ አሉ ። ለቅሷቸውን እንደፍሬን ቀጥ ማድረግ አሳፍሯቸው ነው መሰል ተንፈሳፍሰው ባላዝኖት ዋጡት ።

    ረጭታውና የቤቱ ሰላም የቆየው ግን ለግማሽ ደቂቃ ነበር ። በሰማያዊው ኮመዲኖ ተደብቃባ የነበረችው እጀ'ዱሽ አሻንጉሊት (ታቲ ነው የሚሏት) ላይ አይናቸው እስክታርፍ ። አሻንጉሊቷ የተደበቀችበት ምክንያት መሳይ ጓደኛዋ (ቲታ) ጠፍታ እሷንለሁለቱም ማካፈል ከባድ ስለነበር ነው ።

    ልክ ታቲን እንዳዩ የለቅሷቸው መቀጣጠያ ሌላ ጋዝ ሆነች ። ( *ሰው አይገባውም እንጂ መንታ ማሳደግ አንድአይነት ልብስ ከማልበስ የዘለለ ፖለቲካ ነው ። ዲፕሎማሲ ሳይችሉ እንዴትም የመንታ እናት አይኮንም)

    * * *

    ዛሬ ፥ የመንትየዎቹ ኢዛና'ና ሣይዛና አራተኛ ዓመት የልደት በዓል ነው ። አራቱ ዓመታት ምኔ እንደንፋስ እንዳለፉ ጭራሽ አታውቅም ። የእያንዳንዷ ቀን ርዝመት ግን ማለቂያ አልነበረውም ። ሌት ተኝታ ካደረችበት እንቅልፍ ባይኗ ሳይዞር ያነጋችው ይበልጣል ።

    እንዲህ ያማረ ድግስ በቤቷ ስታዘጋጅ የመጀመሪያዋ ነው ። ሳምንት ሙሉ ስታስብበት ከርማ እንደሚሆን ለማድረግ አንድ ለናቷ የቀረቻትን አምሳ ብር ፈነከተች።

    ቅዳሜ ደርሶ ደሞዝ እስክትወስድ መቆያ ቤስቲን እንደሌላት እያወቀች ለልደታቸው የሚሆኑ ነገሮችን ገዛዝታ እጇ ላይ የቀራት አስራ ስድስት ብር ነው ። ሆኖም ከድግሱ ኋላ ስለሚመጡ ግጥ ቀናት ማሰብ ጭራሽ አትፈልግም ።

    ቲታ (አሻንጉሊቷ) የቆሰቆሰችውን ለቅሶ ገላቸውን በማጠብ ሸውዳ ከሐይቅ የታጨደ ለምለም ገሣ ትጎዘጉዝ ገባች ። መብል ከመደርደሯ ቀድማም የልብስ ሳጥኑን በመጎተት እንደጠረጴዛ የቤቱ መሃል ላይ አኖረችው ። በዘይት የተሟሸ ድስት ውስጥ የዘራችውን ፈንዲሻ በክዳኑ እንዳፈነች አፈካች ። እምትሰራበት ዳቦ ቤት ያስጋገረችውን ኲንስንስ ህብስትም አማትባ ቆራረሰች። ( * ቄስ ቢጠፋ ወንድ … ወንድ ጠፋ ተብሎ ዳቦ ሣይቆረስ አይቀር )

    ይህ ሁሉ ሲሆን የተጠራ ሰው አልነበረም ። ድግሡ የቤተሰብ ነው ፤ የእማይቷና የደቋ ብቻ ። አራት አመት ዝዋይን መባጃ (*ላልቶ ሲነበብ መቆያ እንደማለት) አርጋት ስትኖር ከልጆቿ በቀር ከሰው አክርራ የገጠመችበት ግዜ አታስታውስም ። ጠፍታ እንደመምጣቷና ላገሩ አዲስ እንደመሆኗ አንገቷን አቀርቅራ ወጥታ አፏን እንደለጎመች ትመለሳለች ። ንጭንጯ - መከፋቷ -ማልቀሷ - ሚስጥሯ ፤ ሁሉም በሯን ከዘጋች በኋላ ነው ። ይሄ ፥ ጥሩ የሽቦ አጥር ሰራላት ። እንደ ስውር ክፈፍ እንግዶችን አርባ ክንድ ከሷ አራቀ ። አሁን…ያለፈ ታሪኳን የሚገምት እንጂ የሚያውቅ ባገሩ አንድ አይገኝም።

    ሣራ የፅንስ አፍይ እርሾዋን ዝዋይ አልተቀበለችም ። ወደዝዋይ ከመውለዷ ስምንት ወር ቀድማ ነው የመጣችው። የመጣች ሰሞን የነበራትን ወዝ እንዲ በአራት ዓመት ረግፎ ያልቃል ብሎ የገመተ የለም ። ገላዋ - ደም ግባቷ - የፈገግታዋ ስርጉድ - ከስከሶ ፀጉሯና ድምቡሽ ቂጧ ፤ ለከተማው ገልዋዳ ሁሉ አፍ ማስከፈቻ ነበር ።

    ማርገዟ እየለየ ሲመጣ - ከንፋስ እንደሻለች (*ሽል እንደያዘች) ሁሉ የአባትየውን ማንነት በሆዷ አብታ ኢዛናንና ሣይዛናን ተገላገለች። ጎረባብቶቿም በጀርባዋ ይንሾካሾኩ እንጂ ደፍረው አልጠየቋትም ። ነገሩ 'ምስኪን የማርያም አራስ' ብለው ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ሙያም የላቸው ።

    * * *

    ለሆነ ንግስ (*ለገብርዔል መሰለኝ) ለኩሳው ግማሹ የቀለጠ ሻማን ከመስኮት ጠርዝ አውርዳ ሳጥኑ ላይ አስቀመጠች ። ይህን ያዩት ልጆቿ ለልደታችን አዲስ ሻማ ካልተገዛ የሚል ሌላ ንጭንጭ ጀመራቸው ። ንጭንጩ ወደለቅሶ ከመቀየሩ ቀድማ ወጣችና ሁለት ሻማ ገዝታ ገባች ። ስትመለስ እጇ ላይ አስራ አንድ ብር ቀራት ።

    መዳህና መደገፍ ከጀመሩ ወዲህ ቀኑን ሙሉ ስትጯጯህ ነው የምትውለው ። የልጆቿ ኃይል ግን ከእርሷ በአእላፍ ይበልጣል -የመቶ ባትሪ ድንጋይ ጉልበት ነው ። ሣይዛና አልጋ ላይ ለመውጣት የተነጠፈ አልጋ ከሳበ ኢዛና በጆግ ያለ ውሃ ይደፋል ። አንደኛው የጫማ ሶል አፉ ውስጥ ሲከት አንደኛው የተጣለ ማስቲካ ፀጉሯ ላይ ይለጥፍባታል ። አንዱ ሥኳር በትኖ ከላሰ ሌላኛው ጋወኗ ላይ ኩባያ ደፍቷል ። (*እናት ስድስት እጅ ነው ያላት - ይሉት ተረት ቀልድ አይደለም)

    አንዳንዴ ይደክማታል ። ድካም አይሉት ከባድ ድካም ። አለ አይደል አዙራ የለበሰችውን ቲሸርት አስተካክላ ለማድረግ ሀይል እስከማጣት ድረስ ። ይኼኔ ያለአባባይ ለሰዓት ታለቅሳለች ።በድሎት ተጨንቃ ያደገች ልጅ ሻሽ የክቷ ሆኖ ስታገኘው -በማታቀው ከተማ ያለአንድ ዘመድ ስትኖር - እናትም አባትም ስትሆን - እጣፈንታዋ ከጠርዝ ሲወጣ …እንዴት አታለቅስ ?

    ይዛ የገባችውን ሻማ ለኮሰች ። የለኮሰችበትን ክብሪት ወዝውዛ አጠፋችና እንደማይክ ከአፏ በመደቀን " ክቡራትና ክቡራን የሣራ ተስፋይ ቤተሰቦች - እናታችሁ ለልደታችሁ ሲባል ከኡዝቤኩስታን ካስመጣችው ባንድ ጋር አብራ ታቀነቅናለች " አለች ።

    ሣይዛና ከአፏ ተቀብሎ "ኡዝቤኩቲሲሲዛን እንደኛ መንታ አለ ? …እማዬ " ። ለመልስ ማሰቢያ ግዜ ሳይሰጣት ሌላኛውን ጥያቄ በዛው ቀጠለ ። "እኛ ግን ለምንድን'ነው መንታ የሆነው ?"

    በድካም ውስጥ ሆናም ቅብጠታቸው እንጂ ጥያቄያቸው ሰልችቷት አያውቅም ። " እግዛብሄር ሁላችንንም ሲፈጥር በርሱ አምሳል ነው የሠራን - እና አንዳንዴ የሆነ ፊት ይሰራና በጣም ከወደደው… ይደግመዋል ። ከዛ … መንታ ይፈጠራል ማለት ነው ። " ወሬዋን ጨርሳም እንድትቀጥልላቸው ፊታቸውን እያብለቀለቁ ያይዋታል ። ስትወዳቸው ለጉድ ነው …አታበላልጥም ። ሳይዛና እንቅልፋም ስለሆነ ምናልባት እሱን የበለጠ ሳትወድ አትቀርም። (*ይህን ለመረዳት የመንታ እናት መሆን ያስፈልጋል)

    አይን አይናቸውን እያየች "… ሃፒ በርዝ ደ…'' ከማለቷ

    ከማዳበርያ በተሰራው ኮርኒስ ውስጥ የሚንሸራሸሩት አይጦች መዝሙሯን ለሁለተኛ ግዜ አቋረጧት ። እንዳልበረገገች ሁሉ ራሷን አጀግና " ለ…ሙሽሪት … ማንን ልዳርላት ? " አለቻቸው ። አውቀውባታል ፤ የሷን ያህል አይጥ የሚፈራ በቤቱ የለም ።

    እንደጀርባዋ ታሪክ*(የማይነገር/የማይፃፍ) በዋነነት የምትፈራው ወንድን ልጅ ነው ። ፂም አብቃይ ሁሉ ቀንድ የቀረው አውሬዋ ነው ። የፈጣሪዋ ግፍ ይባስ ጭራሽ ሁለት ተብዓት ከማህፀኗ አሸከማት ። በሆዷ ዓመት ቀረሽ ወራት የፀነሰቻቸውን ....

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message



  • Leoul Zewelde

    የሮም ወታደሮች እየተዟዟሩ
    ሶስቱ ዛይሎኖች ላይ ቅናዋት ሲወቅሩ
    ይታየናል በሩቅ …

    ከካህናት ዕሠይ ፤ ካይሁድ ጉርምርምታ
    አልፎ የሚረብሽ የአንዲት ሴት ስቅስቅታ
    ይሠማናል ከሩቅ …

    ለተጓዥ አላውያን
    መንፈቅ ትርዒት ፥ ከሩቅ ለምናየው
    …የአርብ መንገድ አድክሞን
    ከመስቀሉ ጀርባ ተጋርደን ለቆምነው …

    ክርስትና ርዕዮት ነው !

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • ራቢራ ሱራ ነኝ ። ቢራዬን እንደትኩስ ሻይ ...

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • ውብትሽን ከሩቅ ለሚያይ 'ፍዝ' ነው ። ሎሚ እንዳቤዠው ሻይ ፥ ካልቀመሱት የአይን ስህተት ነው ። ይሄን ብዥታ እንደሀቅ ተቀብለው ፥ ይገፉሻል ። ለእኔ ግን ፥ ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ።

    ከማታውቂው አገር ብትኮምሪ ፥ የቤትሽ የመጨረሻ ሰካራም ፥ እኔ ነው ምሆነው ። ትተሽ ብታዘምሪ ፥ ጭራ ልጌ አጅባለው ። ለእኔ ? ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ።

    በፀጋ ሆነ ቅባት ፥ ብቻ ከአንዱ ሆነሽ ብትነፍቂ ፥ ጥላ ጥለትሽን ይዤ እከተልሻለው ። አንቺ በምታምኚው ፥ እኔ እታነመናለሁ ። ውርስ ሥጋዬ ለስደትሽ ጌተሴማኒ ነው ። ዘመኔን የታነፅኩት ፥ ከሚያሳዱሽ ምስካይ እንድሆን ነው ።

    ከሰው አፍ ውለሽ ፥ ከሰው አፍ ብታድሪ ፥ ገመናቸውን በአንቺ አይተው በመላ አገር ብትነውሪ ፥ ኮሶ እንዳገሳቸው ተጨማደው ቢጠየፉሽ ፥ ያን ገላሽን ወደው በያው ገላሽ ቢከሱሽ ... አንችን አስጠግቼ ነውረኛ እሆናለው ። እነርሱ ከገቡበት ገነት ፥ አንቺ የተጣልሽበት ፥ ደይን እመርጣለሁ ።

    አንቺ ቀርተሽ ፥ ምን ማቅ ኖሮኝ እቀራለሁ ? አግቧቸውን አንገርግሬ ከአንቺው ጋር እጠፋለሁ ። ጣዕምሽን አውልዬ እኔው ነኝ ማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ፤ ከሰው መጥቶ አይደለም ፤ የእውነት ነው ፥ እወድሻለሁ !

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • የተንጣለለው አስፋልት በሚረግፈው የዳመና ቡትርፍ እየታጠበ ነው ። አቶ 'ሀ' ( ይቅርታ ፤ ስሙን ስለማላውቀው  ነው) ጭር ባለው ጎዳና እየተዘነበበት ወደቤቱ ያቀናል ። ተበታትኖ የሚወርደው የጨፈጨፍ ናዳ ሲያርፍ ይዘልና ሌላ  ቀድሞ የወረደ ጨፍ እየያዘ ወደዳር ይንቆረቆራል ። ተርታውን ያቀረቀሩት የመንገድ ዳር መብራቶች ገና ሳይመሽ በስህተት ብርሃናቸውን ወልተዋል ...

    --- Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message
  • የችኮላ ሥራ ሲገጥመኝ ትዝ የምትለኝ ነገር ነች። ቄራ ላይ የሆነ ነው ፥ ያው እንደጨዋታ ። አስኩቲ የሚባል እሳት ሞተረኛ ...

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • ጀግና የወደድሽ ሰሞን ፤ ጀግና አሳድዳለው ። ጎሽ ገድዬ ኮልባ ሎቲ እቀርፃለው ። ከነብር ገላ ላይ ለአንገት በርኖስ እላጫለሁ •••

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • በመሃል እራት አለመብላቴ ትዝ ብሎኝ ደሞ በባዶ ሆዴ ተከዝኩ ። ችግሮቼ በጣም ስለሚወዱኝ ብቻዬን አይተውኝም ፥ አንዱ እንኳ ሲሄድ አንዱን ተክቶ ነው ....

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • ይሄኔ ነው ትርዒቱ የተለኮሰው ። መጀመሪያ የበረንዳው አምፖል ላምባ እንደጨረሰ ኩራዝ ጥር ጥር ሲል ቆይቶ ዚግዛጉ እስኪታይ ድረስ ከሰመ ። ተደፍቶ በስንፍናዬ ያልወለወልኩት ውሃን ወለሉ ሲመጠውና ጠቦ ጠቦ ሲጠፋ አየሁ ። በድንጋጤ እግሮቼን ወንበሬ ላይ ሰበሰብኩ ። የግቢያችን መታጠፊያ ሾላ ዛፍ ላይ የተከመሩ ወፎች ተበተኑ ። እነሱን ተከትለው የዛፉ ፍሬዎች ሿ ብለው ረገፉ ....



    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • በሩ ሁለቴ ተንኳኳ ። ስከፍት የበሩን የውጭ ማዕዘን ተደግፋ ቆማለች ። ሰላምታ ሳትሰጠኝ አልፋኝ ገባችና ዘግቼው ወደሷ እስክዞር ጠብቃ

    " አርግዣለሁ " አለቺኝ ።

    ደንግጬ አየኌት ....

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • የለበሰችው እጅጌ ሙሉ ፒትልስ ወልቆ ምኔ እርቃኗን እንደቀረች አታውቅም ። የተጨመታተረው አንሶላው ሀሩር ገላዋን እየነካ ሲቆጠቁጣት ገልፍፋ ጣለችው ....

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • ከትናንት ወዲያ ማታ ለት እናቴ እሪሪ ብላ እያለቀሰች ገረፈቺኝ ፤ እያነቡ እስክስታ ነገር ። ከደቂቃ በፊት ( ደብተሬላይ ጭረት እስካይና እስክጠይቃት) አገር ጎረቤት ሰላም ነው ብለን ስለ ሙሉ ቁጥሮች ተካፋይ ስታስረዳኝ ነበር ። ድንገትተነስታ ጫማዋን አውልቃ አናት አናቴን እየጠፈጠች < ኧረ ሰዎች አቃተኝ ምናባቴ ላርገው ? > ብላ ለአገላጋዮቼታሳጣኛለች ፤ ሁለተኛ በደል ። ባህሪዋ ለማንም ግራ የሚገባ አይነት ነው ። እስኪ ልፈትናት ብዬ ሁለት ቀን የሚያስቅቀልድ ባወራት ራሱ ትንሽ ፈገግ ሳትል ወደ ጠብደል ምክር ትለውጠዋለች ። ምክሯ ከመብዛቱ የተነሳ አንዳንዴ እንዲሁ <ዛሬ አመክሪኝም ኣ ? > እላታለው ። በራሷ ስቃ ትንሽ ትቆይና < እናት ላይ እንዲ ማሾፍ ጥሩ ነው ? > ብላትጀምራለች . . . ሃሃሃ ..........--- Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • ... ረጅም የስደት ሰልፍ ፥ ሰሌን አናቷ ላይ ጠቅልላ የምትጓዝ እናት ፥ የታረዙ ብላቴኖች ፥ የተደፈሩ መበለት ፥ የተገፈፉ ክብሮች ፥ የከተማ ምሽጎች ፥ የተበሳሱ መስኮቶች ፥ የሚነዱ ቲያትር ቤቶች ፥ ከሰማይ የሚዘንቡ አረሮች ፥ በየቀጠናው የተማገዱ ጎረምሶች ፥ ባንጋ የቀላቸው አናቶች ፥ የሰቀቀን እሪታዎች ፥ ጆፌ የሚዞረው አንገት ፥ የልጁን ሬሳ የሚያናግር አባት ፥ ረጅም የእሾህ አጥር ፥ የስጋት ድንኳኖች ፥ ፈንጂ ዶሿቸው የሚደሁ ገላዎች ፥ እሳት አከፋፋይ ኦራሎች ፥ የነፍሴ አውጪኝ ትርምስ ፥ የሚያለቅሱ ቄሶች ፥ ሚናራቸው የወደቀ መስጂዶች ፥ የተጨነቁ ሩሆች ፥ የማይታይ ነጭ ባንዲራ ...



    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message

  • ሲመሽ – ፊት ላይ የሚለሰልስ ብርትኳናማ የፀሃይ ጨረር ሲፈናጠቅ – ከመስጂድ ሚናር የመግሪብ አዛን ሲሰማ – ህዝቤ ስራ ያንዠረገገው ሚስቶ ፊቱን ይዞ ወደቤቱ ሰከም ሰከም ሲል – የትራፊክና የፍሬቻ መብራቶች መድመቅ ሲጀምሩ – የእራት ወጥ ጢሶች ከየኩሽናው ወደሰማይ ሲወጡ . . .
    ሲመሽ ፤ ሲመሽ . . .
    ትዝ ይለኛል . . . !

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/message