Bölümler
-
ቃልኪዳን ታደሰ በሙያዋ አርኪቴክትና የኢንቴሪየር ዲዛይን ባለሙያ ስትሆን ከካላንድራስ ጋር በነበራት የመጀመሪያው ክፍል ቆይታችን በህይወት ዘመኗ ስለገጠሙዋት ሁነቶች፣ ስለ ህይወት ተሞክሮዋ እንዲሁም ስለቤተሰቦቿና ልጅነቷ እየተጨዋወትን ውብ ቆይታ አድርገናል። ከቃልኪዳን ጋር የነበረን ቆይታ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሲሆን ብዙ ረብ ያላቸው ቁም ነገሮችን ከዳሰስንበት ዘለግ ያለ ጭውውታችን ስለስራዋና ከስራዋ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ያወጋንበት ሁለተኛው ክፍል እነሆ።
ይህንን ክፍል አዳምጣችሁ ስታበቁ እንደተለመደው አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ካላንድራስን ከወደዳችሁት እና ሌሎች በርካቶች ቢሰሙት የሚበጅ ነው የምትሉ ከሆነ ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ወይም ሼር በማድረግ እንዲሁም እና spotify, Apple podcast, Google podcast, Teraki Appን ተጠቅማችሁ የምታዳምጡ ከሆነ RATE በማድረግ እና REVIEW በመጻፍ ልታግዙኝ ትችላላችሁ። -
ቃልኪዳን ታደሰ በሙያዋ አርኪቴክትና የኢንቴሪየር ዲዛይን ባለሙያ ስትሆን በህይወት ዘመኗ ስለገጠሙዋት ሁነቶች፣ ስለ ህይወት ተሞክሮዋ እንዲሁም ስለቤተሰቦቿና ልጅነቷ እየተጨዋወትን ውብ ቆይታ አድርገናል። ከቃልኪዳን ጋር የነበረን ቆይታ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሲሆን ብዙ ረብ ያላቸው ቁም ነገሮችን የዳሰስንበት ዘለግ ያለው ጭውውታችን የመጀመሪያውን በዚህ ክፍል ቀጣዩን ደግሞ በሚቀጥለው ክፍል ይዘንላችሁ የምንቀርብ ይሆናል።
ይህንን ክፍል አዳምጣችሁ ስታበቁ እንደተለመደው አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ካላንድራስን ከወደዳችሁት እና ሌሎች በርካቶች ቢሰሙት የሚበጅ ነው የምትሉ ከሆነ ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ወይም ሼር በማድረግ እንዲሁም እና spotify, Apple podcast, Google podcast, Teraki Appን ተጠቅማችሁ የምታዳምጡ ከሆነ RATE በማድረግ እና REVIEW በመጻፍ ልታግዙኝ ትችላላችሁ። -
Eksik bölüm mü var?
-
ይህ የዛሬው ክፍል የካላንድራስ ፖድካስት 10ኛው ክፍል ሲሆን የዚህ ሲዝን መጨረሻም በዚሁ የሚጠናቀቅ ይሆናል። በምእራፍ ሁለት ደግሞ እንደተለመደው ከሁሉም አይነት የሃሳብ ዘለላዎች የተጠጉ ጥሩ ጥሩ ክፍሎችን ይዤላችሁ በቅርቡ ተመልሼ እመጣለሁ። እስከዚያው ግን መቆያ ይሆናችሁ ዘንድ የዩትዩብ ቻናሌ Mikimac Views ላይ በመሄድ በአይነታቸው ትንሽ ለየት ያሉና አጫጭር ቆይታ ያላቸውን ቪዲዮዎቼን እንድትመለከቱ በተጨማሪም SUBSCRIBE በማድረግ እንደሁልጊዜውም የስራዬ አጋር እና አበርቺ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ።
ወደዛሬው የካላንድራስ ክፍል ስንገባ ስለአሜሪካዊው የስነ ልቦና ባለሙያ Abraham Maslow (አብርሃም ማስሎው) Hierarchy of needs ስለተባለው ቲዮሪው እየተጨዋወትን ቆይታ የምናደርግ ይሆናል። በዚህ የካላንድራስ ክፍል ላይም እንደሁልጊዜው እንግዳ ይዤላችሁ መጥቻለሁ። እንግዳችን ሄኖክ ይባላል።
ኤርትራዊ ሲሆን በአሁን ወቅት ነዋሪነቱ በአሜሪካን ሃገር ነው። የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው በባዮ ኬሚስትሪ የትምህርት ዘርፍ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪውን ደግሞ በፋርማሲ ትምህርት አግኝቷል። ሄኖክ ከትምህርቱ ባሻገር በስነልቦና እና የሰው ልጅ ባህርይ ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች እና ትምህርቶች ቀልቡን እንደሚስቡትና ስለነዚሁ ጉዳዮች ከሰዎች ጋር መወያየት ፣ መጽሃፍትን ማንበብና ፣ ሰርክ አዳዲስ ተያያሽነት ያላቸው ሃሳቦችን መፈለግና ማወቅ ዝንባሌው ነው። ታዲይ ለዛሬም በዚሁ ጉዳይ ላይ የማስሎውን Hierarchy of needs theory ዘርዘር ባለ መልኩ እያጫወተን የሚቆይ የካላንድራስ እንግዳችን ነው።
-
የካላንድራስ ክፍል 9 እንግዳችን አይዳ አብደላ ነች። በመኖር ውስጥ ስለገጠማት አንድ ትልቅ የህይወት መልክ ቀያሪ ክስተት ታጫውተናለች። የአይዳ ታሪክ ለብዙዎቻችን አስተማሪ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም። በታሪኳ ውስጥ ስላለው ጭብጥ እና አንቂ ቁምነገር መናገር ታሪኩን እንዳያበላሸው በሚል ስጋት ብዙ ዝርዝር ውስጥ አልገባም።
ይህንን ክፍል አዳምጣችሁ ስታበቁ እንደተለመደው አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ካላንድራስን ከወደዳችሁት እና ሌሎች በርካቶች ቢሰሙት የሚበጅ ነው የምትሉ ከሆነ ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ወይም ሼር በማድረግ እንዲሁም እና spotify, Apple podcast, Google podcast, Teraki Appን ተጠቅማችሁ የምታዳምጡ ከሆነ RATE በማድረግ እና REVIEW በመጻፍ ልታግዙኝ ትችላላችሁ።
-
በዚህ የካላንድራስ ክፍል ከኢትዮጵያ ኬንያ ከኬንያ ደግሞ እስከ አሜሪካን ሃገር ድረስ የዘለቀና በብዙ የህይወት መልክና ውጣ ውረዶች የተፈተነ ድንቅ የቤተሰብ ታሪክ እንዳሥሣለን። ስደት ፣ ጥንካሬ ፣ ፅናት ፣ በፈተናዎች ያልወደቀ የቤተሰብ ፍቅር ፣ እምነት ፣ ስኬት . . . ብዙ ብዙ ቁምነገሮችን እንማርበታለን ብዬ አስባለሁ።
እንደተለመደው ሃሳብና አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን Instagram እና Telegram ላይ ልትልኩልን ትችላላችሁ።
ይህን ፖድካስት ከወደዳችሁት የምትሰሙበት መተግበሪያ ላይ Rate ብታደርጉልን ምስጋናችን የላቀ ነው።
For more info about Kalandras
www.mikimac.org/kalandras
-
ኢትዮጵያዊነት ማለት ምንድነው?
የኢትዮጵያዊነት ፍቺ ወይም ትርጓሜ እንደያንዳንዳችን የህይወት ትርጓሜና ተሞክሮ የሚወሰን ነው።
አንድ መንገድ ላይ ሊስትሮ እየጠረገ ህይወቱን የሚመራ ልጅ፣ በወሲብ ንግድ የምትኖር አንድ የቡና ቤት ሴት ፣ ስልጣን ላይ ያለ የተመቸው ባለጊዜ ፣ የሃገሩን ዳር ድንበር ለማስከበር ድንበርና ተጋድሎ ላይ ያለ የሃገር ወታደር ፣ የሚጠጣው ውሃ ማግኘት ታላቅ የህይወት ፈተና የሆነበት አንድ አርብቶ አደር ፣ የዝናቡን መዘግየት እያሰበ የጎተራው ባዶነት የሚያስጨንቀው ምስኪን ገበሬ ፣ ለሃገሬ የሚጠቅም ሃሳብ አለኝ በማለቱ ከወህኒ የተጣለው ጋዜጠኝ ፣ የታክሲ የሚከፍለው ገንዘብ በማጣቱ በቀን ብዙ ኪሎ ሜትሮችን በእግሩ እየተጓዘ የሚያስተምረው መምህር ፣ መሪ ነኝ ብለው ገዢ የሆኑና ዘውዱን የጨበጡ እለት ቃላቸውን ቅርጥፍ አድርገው የበሉ ጥጋበኞች በፈጠሩት ጸብ ህይወቱ እየተመሰቃቀለ ያለ የአንድ አካባቢ ህዝብ . . .
እነዚህ ሁሉ እንደጉራማይሌነታቸው ኢትዮጵያዊነትን የሚረዱበት መንገድም ብዙዎቻችን እንግዳ ተቀባይ ፣ የሰው ዘር መገኛ ፣ ሃይማኖተኛ ፣ ወ.ዘ.ተ . . . ከምንለው በእጅጉ የተለየ ነው።
የዚህ የፖድካስት ክፍል አላማም መስማማት ላይ እንድንደርስ ወይም ለቃሉ ፍቺ የሚሆን ሃሳብ ላይ ተስማምተን እንድንለያይ ሳይሆን እስከዛሬ ይዘን የመጣነውን እውነት እንድንሞግትና የውስጥ ጥያቄዎቻችንን አውጥተን እንድንወያይበት ታሳቢ በማድረግ የቀረበ ነው::
ሃሳብ አስተያየታችሁን ላኩልን።
Follow us on INSTAGRAM and TELEGRAM
-
ዮሐንስ ሞላ "የብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" የተሰኙ ሁለት የግጥም መጽሃፍትን ያሳተመ ገጣሚ ሲሆን በዚህ 6ኛው የካላንድራስ ፖድካስት ክፍል የተለያዩ ጉራማይሌ ሃሳቦችን እያነሳን የተጨዋወትንበትን ቆይታ እነሆ!!
ሃገር ፣ ማንነት ፣ ሞት ፣ ፍቅር ፣ ገንዘብ . . . በርከት ያሉ ሃሳቦችን እንዳሥሣለን።
⚠️በዚህ ፖድካስት ላይ "የብርሃን ቀለማት" በሚል የተጠቀሰው አንደኛው የዮሐንስ ሞላ መፅሃፍ ርእስ በስህተት ሲሆን "የብርሃን ሰበዞች" በሚል እንዲታረም እንጠይቃለን::
ከታላቅ ይቅርታ ጋር 💛🙏 -
ሴት ልጅን ለማክበርና የሚገባትን ሁሉ ታገኝ ዘንድ የአቅማችንን ሁሉ መጣር አለብን። ይህ ደግሞ ሰበብና ምክንያት አይፈልግም። ሴት እናት ፣ እህት ፣ ሚስት ፣ ሃገር . . . ስለሆነች ሳይሆን እንደኔ ፣ እንዳንተ ፣ እንደ እኛና እንደሁላችን ሰው ስለሆነች ብቻ . . .
-
ሃይማኖት ምንድነው? እምነትስ እንደምን ያለ ነው? ጥቅምና ጉዳትስ ይኖራቸው ይሆን? በዛሬው የካላንድራስ ክፍል ሃይማኖትና እምነትን ፣ የሰዎችን የህይወት ልምምድ እና እይታ እንዳሥሣለን። ይህ ኢፒሶድ በClubhouse የካላንድራስ ክፍል ከተደረገ የሰዓታት ውይይት ላይ ለፖድካስት እንዲያመች ተደርጎ ተመጥኖ የቀረበ ነው።
ካላንድራስን Rate ያድርጉ። ለወዳጆቻችሁ አጋሩልን። እጅግ ከላቀ ምስጋና ጋር።
ልዩ ምስጋና - ለትእግስት ሁሴን 💛💛💛
-
ሰርፀ ፍሬስብሃትን ብዙዎቻችን የምናውቀው በሙዚቃ ባለሙያነቱ ነው። ከሙዚቃው ባሻገር ለየት ያለ የህይወት መረዳት ካላቸው ሰዎችም አንዱ ነው። በዚህ Episode "የሰው ልጅ ፍጥረቱ እንደምን ያለ ነው?" በሚለው ዙሪያ ያደረግነውን ቆይታ እነሆ።
-
በራስ መተማመንን እንዴት እንረዳዋለን? በራሴ እተማመናለሁ ለማለትስ መስፈርቶቹ ምን ይሆኑ? በራስ ከመተማመን ጋር ተያይዞ ያለንን መረዳት ከተለያዩ አንጻሮች ለመመልከት እንሞክራለን። በዚህ የፖድካስት ክፍል ላይ በራስ ስለመተማመን ሃሳባቸውን የሚያጋሩን ተሳታፊዎች ይኖሩናል። ይህ የፖድካስት ክፍል ክለብ ሃውስ ላይ ከተደረገ የ5 ሰዓታት ውይይት ላይ ለፖድካስት እንዲያመች ተመጥኖ የቀረበ ሲሆን ሙሉውን ውይይት ለማድመጥ የምትፈልጉ ከታች የተቀመጠው ሊንክ ላይ ታገኙታላችሁ።
https://www.clubhouse.com/room/xnbLQWd4
ካላንድራስን Rate ያድርጉ። ለወዳጆቻችሁ አጋሩልን። እጅግ ከላቀ ምስጋና ጋር።
ልዩ ምስጋና - ለትእግስት ሁሴን 💛💛💛
-
ኢታና ነዋሪነቱ በአሜሪካን ሃገር የሆነ ጎበዝ ሙዚቀኛ ፣ የቤተ ክርስቲያን ዘማሪ እንዲሁም በስነ መለኮት ፣ ሂሳብ እና የቴክኖሎጂ ትምህርቶች የተጋ ኢትዮጵያዊ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ባለትዳር እና የ2 ልጆች አባት ነው።
ኢታና በካላንድራስ ስለህይወት አረዳዱ ፣ ስለቤተሰቦቹ ፣ ስለ privillege እና በህይወት ውስጥ ከሚገያጋጥሙ ልዩነቶች ጋር እንዴት እያመቻመቸ እንደሚያልፍ ያጫውተናል። -
This is KALANDRAS. A vibecast
We share vibes, sharing what we know from eachother, breaking taboos, questioning society . . . BZU BZU